Fana: At a Speed of Life!

ለኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ75 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ማሽነሪ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ75 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ማሽነሪ ከጀርመን ልማት ደርጅት ድጋፍ ተደረገ፡፡
በርክክብ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደተናገሩት ÷በወራሪው ቡድን ህወሓት የወደሙትን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች በፍጥነት መልሶ በማቋቋም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያበረክቱትን አስተዋፆን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡
ድጋፉ ለፖሊ ቴክኒኩ ለቴክስታይል፣ ለኮንስትራክሽን እና ግብርና ኮሌጆች አገልግሎት የሚዉል ሲሆን÷ድጋፍ ላደረገው ተቋምም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የጀርመን ልማት ድርጅት ተጠሪ ሚኒስትር ሮበርት ሆልመር በበኩላቸው÷ ድጋፉ ኮሌጁ ከደረሰበት ውድመት አገግሞ ወደ መማር ማስተማር እዲገባ ድርሻው ትልቅ ነው፤ በቀጣይም ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ መላኩ አራጋው ተቋሙ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ጠቅሰው ይህ ድጋፍ ትምህርት ለመጀመር ትልቅ ድርሻ አለው፤ በቀጣይም ሌሎች ተቋማት ድጋፍ እዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡
በሰብለ አክሊሉ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.