Fana: At a Speed of Life!

ብልፅግና ፓርቲ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልፅግና ፓርቲ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም በጅግጅጋ ከተማ መገምገም ጀምሯል።

መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የብሔራዊ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፓርቲው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እቅዱ መሠረት በቅድመ ምርጫና በምርጫው ወቅት የነበረውን አፈጻጸም ይገመግማል፣ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን ይለያል፣ በድህረ ምርጫ ወቅትም ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.