አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያውን ይፋዊ የትውውቅ መድረክ እያከናወነ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያ ይፋዊ ትውውቅ ሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሰላም እናቶች ጋር እያደረገ ነው።
በስነ ሰርዓቱ 11ዱ ኮሚሽነሮች ከሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አባ ገዳዎች እና የሰላም እናቶች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
በዚሁ ጊዜ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ፤ አባ ገዳዎች እና እናቶች የሰላም መልዕክት አሰተላልፈዋል።
የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎቹ ኮሚሽኑ በስራው ስኬታማ እንዲሆን እንደሚደግፉም አስታውቀዋል ።
በዓላዛር ታደለ እና በበላይ ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!