ለ”ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሃገር ቤት” ጥሪ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው
በዚህም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራው ነባሩ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተገልጿል።
ጉዳዩን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በሰጡት መግለጫ ፥ “ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሃገር ቤት” ጥሪ መርሃ ግብር ለወራት የሚዘልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ሃገራዊ ጥሪው በታቀደ እና በተደራጀ መልኩ በመምራት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ የጎረቤት ሃገራት እና የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ዜጎች የዒድ አልፈጥር በዓልን በኢትዮጵያ እንዲያከብሩ በማድረግ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግቦችን ለማሳካት ታስቧልም ብለዋል።
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው ፥ ጥሪው በስኬት እንዲጠናቀቅ እና ውጤታማ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችን መወጣት ይጠበቅብና ብለዋል፡
ዳያስፓራውም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
አረንጓዴ አሻራ፣ የኢንቨስትመንት ኢግዚቢሽን ፣ሃገር አቀፍ የንግድ ትርኢት እና ባዛር፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እንዲሁም ታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ፣ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መጎብኝት እና ድጋፍ፣ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ እንዲሁም ሌሎች መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩም ታውቋል ።
በምንይችል አዘዘው