ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ መጠን ይፋ አደረገ፡፡
ቦርዱ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያካሄደ ሲሆን÷ ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠንን ይፋ አድርጓል።
የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
ለ19 አገር አቀፍ እና 35 የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምሩ ለ54 ፓርቲዎች እስከ 789 ሺህ ብር የሚደርስ ድጋፍ እንደሚደረግ ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!