Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ አንታሊያ በሚካሄደው የኤሮዢያ የዓየር ላይ ትርዒት ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ግብዣ ቀረበላት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሕዳር ወር በቱርክ አንታሊያ በሚካሄደው የኤሮዢያ የአየር ላይ ትርዒት ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ተጋበዘች፡፡

በቱርክ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አደም መሀመድ የኤሮዢያን የዓየር ላይ ትርዒት አመራር ሀካን ኩርት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በአቪየሽን ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሕዳር 16 እስከ 20/2022 በቱርክ አንታሊያ በሚካሄደው የኤሮዢያ የዓየር ላይ ትርዒት ኢትዮጵያ ተሳታፊ እንድትሆን ግብዣ መቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኤሮዢያ የዓየር ላይ ትርዒት ላለፉት 12 ዓመታት በቱርክ ፣ በቱሪዝም መዳረሻነት በምትታወቀው አንታሊያ ሲካሄድ የቆየ እና በአቪየሽን እና ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ ሁነት ሲሆን ÷ በፈረንጆቹ 2018 በተካሄደው ሁነት ላይ 63 ሀገራት፣ 213 የተለያዩ አመራሮችና በዘርፉ የተሰማሩ ዓለም አቀፍና በቱርክ የሚገኙ ግዙፍ ኩባንዎች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.