Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ5 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የሙያ ሥልጠና መውሰድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከ5 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ወደ ስራ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡
ስልጠናው የአጭር ጊዜ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ሲሆን በከተማዋ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ 5 ሺህ 207 ስራ ፈላጊ ወጣቶችን ያሳተፈ ነው፡፡
የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ÷ስልጠናው ወጣቶች በቆይታቸው ተገቢውን ዕውቀት ይዘው በመውጣት ወደ ስራ ሲሰማሩ እራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ያግዛል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሰልጣኝ ልማት ዳይሬክተር ታደለ አየነው እንደገለጹት÷ በአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለማሰልጠን በተቀበሏቸው 740 ወጣቶች ስልጠናው በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።
ስራ ፈላጊ ወጣቶች በ14 የቴክኒክ ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጆች በመረጡት ሙያ በቆዳና የቆዳ ስራዎች፣ በጨርቃጨርቅ፣ በአውቶሞቲቨ፣ በሆቴል ቱሪዝም፣ በፈርኒቸር፣ በቢዝነስ፣ ኮንስትራክሽን፣ በግብርና፣ ማኑ ፋክቸሪንግ እና በሌሎች ሙያዎች እንደሚሰለጥኑ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.