Fana: At a Speed of Life!

የግንባታ ዝግጅት ከተጀመረለት 9 ዓመት ያለፈው የአየር ጤና- ሰበታ መንገድ ዛሬም ግንባታው አልተጀመረም

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግንባታ ዝግጅት ከተጀመረለት 9 ዓመት ያለፈውና ባለፈው መስከረም ይጀመራል ተብሎ የነበረው የአየር ጤና- ሰበታ መንገድ ግንባታ ዛሬም አለመጀመሩን ጣቢያችን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ታዝቧል።

በመንገዱ ዙሪያ ዘገባ ሰርቶ የነበረው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን ባናገረበት ወቅት ፥ መንገዱ የአዲስ – ሰበታ -ጊቤ በሚል በጀት ተይዞለትና ዲዛይኑ አልቆ እንደሚጀመር ገልጾ ነበር።

ጣቢያችን አሁንም መንገዱ ያለበትን ሁኔታ ባጣራበት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የአለምገና መንገድ ኔትወርክና ደህንነት አስተዳደር ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አህመዴ ሙህዬ ፥ የአየር ጤና ወለቴ መንገድ የሚመለከተው የአዲስ አበባ መንገዶች አስተዳደርን በመሆኑ ከወለቴ ጀምሮ እስከ ጊቤ ያለውን መንገድ አስጀምረናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታከለ ሉለና በበኩላቸው ፥ መንገዱ ለዓመታት የህብረተሰቡ ቅሬታ ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ሆኖም በጀት ስለሌለንና የወሰን ማስከበሩም ስላልተጠናቀቀ የመንገዱን ግንባታ በዘንድሮ ዓመት ለማስጀመር አንችልም ብለዋል።

ከዘጠኝ ዓመታት በላይ በዲዛይን፣ በጀት እና ሌሎች ችግሮች እየተሰየሙለት በባለቤትነት ሊተገበር ያልቻለ መንገድ ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ይሆን ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ፥ መንገዱን በሚቀጥለው ዓመት እቅድ ውስጥ በማስገባትና በጀት በማስፈቀድም እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.