የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ30 ቀናት የሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ30 ቀናት የሚጠናቀቁ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን አስጀምሯል፡፡
ፕሮጀክቶቹ በዋናነት የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማደስ፣ በክፍለ ከተማው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች የዳቦ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ፣ የከተማ ግብርና ማስፋፋትንና የእሁድ ገበያን ማጠናከር የሚሉትን ያቀፉ ናቸው።
የተጀመረው መርሃ ግብር ዋና አላማ÷ ባለሀብቱን በማስተባበር ከ57 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሶስት የዳቦ መጋገሪያ ማሽንና ሱቆችን ገንብቶ ለተጠቃሚው ማስተላለፍ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ተናግረዋል።
ስራ አስፈጻሚዋ ከክፍለ ከተማው ባለሀብት ጋር በመተባበር የህብረተሰቡን ኑሮ የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን አስጀምረናል ብለዋል።
በዓለምሰገድ አሳዬ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!