Fana: At a Speed of Life!

ሕዝቡ የጸረ ሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መጥቷል – ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጸረ ሙስና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ሕዝቡ የጸረ ሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መጥቷል አሉ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም ለቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመው 17ኛው ሀገር አቀፍ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ በአዳማ ተካሂዷል።

ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፉት ዓመታት ሙስናን ለመዋጋት የትውልድ ሥርዓት ግንባታ ላይ በትኩረት ተሰርቷል፡፡

በዚህም በፀረ ሙስና ትግል ዙሪያ በተሰራ ግንዛቤ የማስረጽ ስራ ሕዝቡ የሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

መንግሥት በሙስና ላይ የያዘው አቋምና እየወሰደው ያለው ርምጃ ሙስናን ለመዋጋት የሚደረገውን ትግል ውጤታማ እያደረገው ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ኮሚሽኑ በፀረ ሙስና ትግሉ በሥነ ምግባር ግንባታ፣ ሙስናን አስቀድሞ መከላከልና በሕግ ማስከበር ረገድ ውጤታማ አፈጻጸም አስመዝግቧል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.