ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሶማሊያ እና ጅቡቲ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ እና ጅቡቲ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባሳለፍነው ሐሙስ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ሶማሊያ ሞቃዲሾ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለትም በሶማሊያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጅቡቲ ሲደርሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቆይታቸውም በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ እና ጅቡቲ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡