Fana: At a Speed of Life!

አቶ አህመድ ሺዴ ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር ማቲልዳ ኧርንክራንስ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው በሁለትዮሽ በተለይም በሀገራቱ መካከል የልማት ትብብር ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።
በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያ ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ባለው ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
ከዚህ ባለፈም በተከሰተው ድርቅ እና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት መተላለፊያ መስመርን እንዲኖር ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከት ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ እና በሰላም ሂደቱ ለሚታየው አወንታዊ መሻሻል አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም ስዊድን ልማትና ሰብአዊ ድጋፉን ለማስቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.