አቶ ሙስጠፌ አልሸባብን ለመደምስ ከክልሉ ልዩ ኃይል ጋር የተቀላቀለውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አሸባሪውን አልሸባብ ለመደምስ ከሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ጋር የተቀላቀለውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ጎብኝተዋል።
የአሸባሪውን አልሸባብ ታጣቂዎችን እየደመሰሰ የሚገኘውን የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ለማገዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዘመቻውን የተቀላቀለ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሰሞኑን “አቶ” በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሾልኮ የገባው የአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን “ሁልሁል” በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበበ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ መደምሰሱን የክልሉ መንግስት የፀጥታ ምክር ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።
ለሦስት ቀናት በተካሄደው ዘመቻም ከ100 በላይ የአሸባሪው ቡድን አባላት ሲገደሉ÷ አሸባሪው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ 13 ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው ተገልጿል፡፡