Fana: At a Speed of Life!

4 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን የሚመዝኑ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች መቀሌ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 4 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን የሚመዝኑ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች በአውሮፕላን መቀሌ ከተማ መድረሳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

መቀሌ ከገቡት የህክምና ግብዓቶች ውስጥ 3 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን የአደጋ ጊዜ ቀዶ ጥገና ኪቶች እና 1 ሜትሪክ ቶን የቲቢ በሽታ መድሃኒቶች እንደሚገኙበት ከዓለም ጤና ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቲቢ በሽታ መድሃኒቱ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የተላከ ሲሆን፥ የአደጋ ጊዜ ቀዶ ጥገና ኪቶች ደግሞ በዓለም ጤና ድርጅት እርዳታ የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የህክምና ግብዓቶቹ በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ድንገተኛ የቀዶ ሕክም አገልግሎትን እና የቲቢ በሽታ ታማሚዎችን ለማከም የሚደረገውን ጥረት መደገፍ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.