Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ በተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አማካኝነት በድርቅ ለተጎዱ አራት  ክልሎች የሚሰራጭ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ይህም በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ለአስከፊ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ህጻናትን መታደግ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለአስከፊ የምግብ እጥረት ለተዳረጉ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ እየሰራ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.