Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በ2014 በጀት ዓመት የተያዙ የልማት እቅዶችን አሳክቻለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮችን በመቋቋም በ2014 በጀት ዓመት የተያዙ የልማት እቅዶችን ማሳካት መቻሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በበጀት ዓመቱ ለ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩንና የክልሉ ኢኮኖሚ በ6 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በበጋ የመስኖ ስንዴ በ2ኛ ዙር 327 ሺህ 636 ሄክታር መሬት በማልማት 14 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ማምረት መቻሉንም የኦቢኤን ዘገባ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.