አምባሳደር ነቢል ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ከሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንትና የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ታባን ዴንግ ጋይ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
አምባሳደር ነቢል የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ውስጥ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አምባሳደሩ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ የታዩ አበረታች ለውጦችን አድንቀዋል።
ሁለቱን ሀገራት በመንገድ ለማስተሳሰር የተጀመረውን ጥረት በማድነቅ÷ ፕሮጀክቶቹ እንዲሳኩ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንት ታባን ዴንግ ጋይ በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያ ሰላም መረጋገጥ ለአካባቢው በጎ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመግለጽ መንግሥት ለዘላቂ ሰላም መስፈን ለጀመረው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
የመንገድ መሰረተ-ልማቱ ሁለቱን ሀገራት ከማስተሳሰር በዘለለ ለአካባቢያዊ ውህደት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለመንገዱ ስኬታማነት ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥል መጠየቃቸውንም በደቡብ ሲዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!