የአፋር ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ዛሬ ተጠናቋል።
ጉባኤዉ በዛሬዉ 4ኛ ቀን ዉሎ የክልሉን የአስፈጻሚ አካላትን ተግባርና ሃላፊነት እንደገና ለማደራጀት የተዘጋ ረቂቅ አዋጅ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ፋጡማ መሀመድ ለምክር ቤቱ በንባብ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም የቀረበዉ የአስፈጻሚ አካላት ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።
በዚሁ መሰረት እንደ አዲስ ለተዋቀሩት ሶስት ቢሮዎች የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተሿሚዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ምክር ቤቱም አቶ አሊ ባሂና አሊ የክልሉ ማዕድን ሀብት ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ወላህ ውቲካ የክልሉ የተፋሰስ ልማት ቢሮ ሃላፊ እና አቶ ሃሚድ ዱላ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሆኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ያቀረቡትን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ተሻሚዎቹም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-መሃላ መፈጸማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በተጨማሪም የአፋር ክልል ምክር ቤት በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቅራቢነት 34 የወረዳ እና 5 የዞን ፍርድ ቤት ፕሬዚዳቶችን ሹመት መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!