Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምሥራቅ ሸዋ የለማውን የስንዴ ማሳ ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦራ እና ዱግዳ ወረዳዎች በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የስንዴ ምርት ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም ከውጭ የሚመጣውን ስንዴ ለማስቀረት በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በምሥራቅ ሸዋ ዞን በዘንድሮ የመኸር እርሻ 439 ሺህ 120 ሔክታር እየለማ ሲሆን÷ ከዚህም 184 ሺህ 309 ሔክታሩ በኩታ ገጠም የስንዴ ሰብል የለማ መሆኑን ኦቢን ዘግቧል፡፡
በስንዴ ልማት የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማጎልበት በተከናወነው ሥራ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.