998 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 998 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡
ከተመላሾቹ ውስጥ 985 ወንዶች ሲሆኑ አንድ ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ 12 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ 62 ሺህ 447 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡