Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንዷ ዘ ሄግ ከተማ ከሩሲያ ጋዝ የመግዛት እገዳ ነፃ መሆን ትሻለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መቀመጫ የሆነችው የኔዘርላንዷ ከተማ ዘ ሄግ ከሩሲያ ጋዝ መግዛት የሚያስችላትን ጊዜያዊ ፈቃድ ከአውሮፓ ኅብረት ለማግኘት እንደምትሻ አስታወቀች።

የኔዘርላንዷ ዘ ሄግ ÷ ለጊዜውም ቢሆን ፈቃድ የምትጠይቀው አማራጭ የኃይል አቅርቦት ባለማግኘቷና ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ባለመቻሏ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከተማዋ ለአውሮፓ ኅብረት የምታቀርበው ጥያቄ ኅብረቱ በሩሲያ ላይ ከጣለው ማዕቀብ ለጊዜው ነፃ እንድትሆን ያስችላታል ነው የተባለው፡፡

ዘ ሄግ ጥያቄዋ ተቀባይነት ካገኘ፥ አማራጭ ኃይል አቅራቢ እስክታገኝ ድረስ ከሩሲያው ግዙፍ ጋዝ አቅራቢ “ጋዝፕሮም” መግዛት ትችላለች ነው የተባለው፡፡

የሄግ ከተማ ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ ዕቅዱን በምክትል ከንቲባዋ ሳስኪያ ብሩንስ በኩል ለማዘጋጃ ቤቱ በጽሑፍ አቅርቧል፡፡

የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ባለስልጣናት ባሳለፍነው ሰኔ እና ሐምሌ ወር ላይ በአውሮፓ ኅብረት ደረጃ የጋዝ አቅራቢ ለማግኘት ጨረታ ቢያወጣም እንዳልተሳካላቸው በቀረበው ጽሑፍ መጠቀሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ኅብረቱ ሩሲያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ሁሉም የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት እስከ ፈረንጆቹ ጥቅምት 10 ድረስ ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር ያላቸውን ውል በማቋረጥ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

እስካሁን የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ዘ ሄግ ባቀረበችው ጥያቄ ላይ፥ ያለው ነገር እንደሌለም ተገልጿል፡፡

ዘ ሄግ የአውሮፓ ኅብረት ሩሲያ ላይ ከተጣለው ማዕቀብ በተቃራኒ ይህን መሰል ጥያቄ ያቀረበች የመጀመሪያዋ ከተማ መሆኗን የአር ቲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.