በመዲናዋ 3 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 3 ቢሊየን ብር ገደማ ወጪ የሚደረግባቸው ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር ከሦስት ተቋራጮች ጋር የኮንትራት ስምምነት ተፈረመ፡፡
የመጀመሪያው ከአፍሪካ ጎዳና – ኤድናሞል አደባባይ – 22 ማዞሪያ – እንግሊዝ ኢምባሲ የሚዘልቀው እጅግ ዘመናዊ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን “ኢንተለጀንት ትራንስፖርት ሲስተም” (ITS) ያካተተ ነው፡፡
የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዝ ፕሮጀክት ሲሆን፥ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የሚገነባ ነው፡፡
ሁለተኛው የአየር ጤና – ወለቴ ሱቅ – ዓለም ገና አደባባይ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ነው፡፡
ሦስተኛው የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ መላው የከተማችን ነዋሪዎች እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን ሁለንተናዊ እድገትና ገፅታ በእጅጉ የሚቀይሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ለፕሮጀክቶቹ ስኬት ከወሰን ማስከበር ስራው ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር ህዝቡ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!