Fana: At a Speed of Life!

ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ኢትስዊች የክፍያ ስርዓትን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ኢትስዊች የተባለውን የንግድ ባንኮች የሚገኙበትን የክፍያ ስርዓት ተቀላቀለ።

ሁለቱ ተቋማት ዛሬ ተፈራርመዋል፡፡

የካቻ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ከባንክ፣ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ፣ ኢንሹራንስ፣ ብድርና እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመተባበር በሀገሪቱ በሚገኙ 30 ሺህ ወኪሎች አማካኝነት ከጥሬ ገንዘብ ነፃ የሆነ ግብይት ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል።

አገልግሎቱ ኢትስዊችን በመቀላቀሉ ተደራሽነቱን እንዲያሰፋ እና ደንበኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚረዳ ተገልጿል።

ካቻን በመጠቀም የሞባይል ሂሳብ መክፈት፣ በወኪሎችና ሌሎች አማራጮች በመጠቀም ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ፣ አነስተኛ ቁጠባ፣ ብድሮች፣ የኢንሹራንስ አገልግሎቶች፣ የቀጥታ ክፍያዎች እና ዓለም አቀፍ ኃዋላ ማከናወን እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ለገንዘብ ማስተላለፍ፣ የሞባይል አየር ሰዓት ፣ የኤቲኤም ክፍያ ካርዶች እና ጥሬ ገንዘብ-አልባ ግብይቶችን መከወንን ጨምሮ ሌሎች ህይወትን ሊያቀሉ፣ ለኑሮው መሻሻል ሊጠቅሙ የሚችሉ አዳዲስ አገልግሎቶችን ያካትታል ነው የተባለው፡፡

ተቋሙ ወደገበያ ለመውጣት የሙከራ ትግበራ እያካሄደ መሆኑ ተመላክቷል።

ካቻ ዲጂታል የፋይናንሺያል አገልግሎት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት አቅራቢ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.