ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሎግያ ሆስፒታል የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል ኤይድ ኢትዮጵያ ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሎግያ ሆስፒታል ግማሽ ሚልየን ዶላር የሚገመት ዘመናዊ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ድጋፍ አደረገ።
የግሎባል ኤይድ ኢትዮጵያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መላኩ ሥዩም ድጋፉን ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሐመድ ዑስማን አስረክበዋል።
በወቅቱ ዶክተር መሐመድ ÷ ድጋፉ የብዙ ወገኖችን ችግር የሚፈታ መሆኑንና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፤ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ መላኩ ሥዩም በበኩላቸው ÷ድርጅታቸው መሰል ድጋፍ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም አንድ ኮንቴይነር የተለያዩ ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁሶች ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሎግያ ሆስፒታል ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!