በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተከናወኑ የሠላምና ጸጥታ ሥራዎች ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተከናወኑ የሠላምና ጸጥታ ሥራዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
የምክክር መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልል የሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደር፣ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ከፍተኛ አዛዦች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በመድረኩም በክልሉ ባለፉት ወራት በሶስቱም ዞኖች፣ በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ፣ በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የተከናወኑ የሠላምና የጸጥታ ሥራዎች ቀርበው እንደሚገመገሙ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም በቀጣይ የክልሉን ሠላምና ጸጥታ የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ የቀጣይ አቅጣጫዎች በመድረኩ እንደሚቀመጡም ይጠበቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!