ከተማ አስተዳደሩ 200 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘርና ሳሙና ወደ ከነማ የመድሃኒት መደብሮች እያስገባ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን የንጽህና መጠበቂያዎቹን ወደ ከነማ የመድሃኒት መደብር የማስገባት ስራ ላይ ተሳትፈዋል።
ህብረተሰቡ ከነገ ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ በሁሉም የከነማ መድሃኒት መደብሮች በመገኘት አንድ ሊትር ሳኒታይዘር በ80 ብር እንዲሁም 250 ሚሊ ሊትሩን ደግሞ በ40 ብር መግዛት እንደሚችሉ የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
መግዛት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ የልየታ ስራ በመስራት የከተማ አስተዳደሩ ሳኒታይዘሮቹን ለተጠቃሚዎች በነጻ የሚያቀርብ መሆኑንም ገልጿል።