Fana: At a Speed of Life!

የኩላሊት እጥበት ለማድረግ አቅማቸው ለማይፈቅድ የመዲናዋ ነዋሪዎች 20 ሚሊየን ብር ተመደበ 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመትከፍለው የኩላሊት እጥበት ማድረግ ለማይችሉ ዜጎች 20 ሚሊየን ብር መመደቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል በመንግስትና የግል ሴክተሩ አጋርነት የኩላሊት እጥበት ማእከል ማቋቋሙ የሚታወስ ነው፡፡

አስተዳደሩ የማዕከሉን ህንጻ  ከማመቻቸት ጀምሮ ሰራተኞችን በመቅጠር እንዲሁም የአብ ሜዲካል ማዕከል የኩላሊት እጥበት ማሽኖቹን በማቅረብ እና ሌሎች ሙያዊ እገዛ በማድረግ በጋራ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል፡፡

በማዕከሉም የከተማ አስተዳደሩ በ2015 ዓ.ም ከአብ ሜዲካል ሴንተር ጋር በመተባበር ከፍለው የኩላሊት እጥበት ማከናወን የማይችሉ ወገኖችን ወጪ ለመሸፈን 20 ሚሊየን ብር መመደቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.