በቢሾፍቱ በ133 ሚሊየን ብር የተቋቋመው ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ በ133 ሚሊየን ብር የተቋቋመው ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር የግብርና መሳሪያዎች መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ።
ፋብሪካው ለመስኖ ልማት የሚያግዙ የውሃ መሳቢያ (ፓምፕን) ጨምሮ ለግብርና ምርት አጋዥ የሆኑ የግብርና መሳሪያዎች ያመርታል ተብሏል፡፡
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ተገኝተዋል።
ከፋብሪካው ምርቃት በተጨማሪ 16 ሺህ 803 የመስኖ ፓምፖች ለአርሶ አደሮች ተከፋፍለዋል፡፡
የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ በዚሁ ወቅት በገጠር ልማት ዘርፍ አራት ዋና ግቦችን አቅዶ እየሰራ መሆኑ በዚህ ወቅት ተገልጿል።
በአዳነች አበበ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!