Fana: At a Speed of Life!

የሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በካናዳ የተወለዱ ሕጻናትና ታዳጊዎች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ያካተተ 120 አባላት ያሉት የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ አገልግሎት አቀባበል ተደርጎለታል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ለአንድ ወር በሚኖራቸው ቆይታ በባሕል ልውውጥ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ሲሆን÷ ታሪካዊ ቦታዎችንም ይጎበኛሉ።

የልዑኩ አስተባባሪ አሸናፊ ግርማ÷ አባላቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በተለይም ለኢትዮጵያውያን ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾች ያላቸውን ልምድ እንደሚያካፍሉ ተናግረዋል።

የልዑኩ አባላት በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን ባሕልና ታሪክ በሚገባ ከመረዳት ባለፈ ከሀገራቸው ታሪክ፣ ባሕልና ማንነት ጋር ያላቸውን ትስስር እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

መርሐ ግብሩ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ይበልጥ እንዲያውቁና የባሕል ትስስራቸውን  እንዲያጠናክሩ የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል።

በጀማል አሕመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.