በጎንደር ከተማ ለጥምር ጦሩ 17 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር ለጥምር ጦሩ ድጋፍ በዓይነትና በጉልበት 17 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡
የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዮ አቡሃይ በድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት የከተማው ህዝብ ለጥምር ጦሩ 17 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነትና የጉልበት ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአድርቃይ እና በወፍ አርግፍ ግንባር እንዲሁም በጎንደር ከተማ 2 ሆስፒታሎች ለሚገኙ ቁስለኞች ድጋፉ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል ።
የከተማው ህዝብ በስንቅ ዝግጅት እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጠቆሙት ምክትል ከንቲባው፥ ከስንቅ ዝግጅት ጎን ለጎን የከተማው ህዝብ ተደራጅቶ አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል ።
የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የህብረተሰቡ የደጀንነት ተግባርም አሸባሪው ህወሓት እስከሚደመሰስ ድረስ ሊቀጥል ይገባልም ነው ያሉት ፡፡
በአበራ መኮንን