በአሸባሪው ህወሓት ለተጎዱ ዜጎችና ተቋማት 5 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎችና የጤና ተቋማት 5 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ አስታውቋል፡፡
ድጋፉ በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችና የጤና ተቋማት ተደራሽ መደረጉ ተገልጿል፡፡
የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ ፕሬዚዳንት ዶክተር ትሁት አስፋው እንደገለጹት÷ ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ በተዘጋጀው የቤተ መንግሥት የእራት ግብዣ ከ800 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብ ተሰብስቧል፡፡
ማህበሩ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ለመደገፍ 3 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር ማስረከቡን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
የካናዳ መንግስት የስራ ኃላፊዎችና የፓርላማ አባላትን በደብዳቤና በዙም ስብሰባ በማግኘት በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማህበሩ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡
በዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን በማገዝ ረገድ የጀመሩትን ሥራ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!