Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ለዶክተር ካትሪን ሀምሊን ስንብት አደረጉ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለዶክተር ካትሪን ሀምሊን በመኖሪያ ቤታቸው በመገኘት ስንብት አደረጉ።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን ድንጋጌዎች በመተግበር፥ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት ዶክተር ካትሪን ሀምሊን መኖሪያ ቤት በመገኘት ስንብት አድርገዋል።

ለዶክተር ሀምሊን ልጅ የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልጹም፥ ዶክተር ሀምሊን ለአካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ከሚዳርገው የፌስቱላ ችግር ከ60 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን የታደጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም ለዓመታት ያስተማሯቸውና ያሰለጠኗቸው በርካታ ባለሙያዎች ዶክተር ሀምሊን ሥራውን በጀመሩበትና በመሠረቱት ብቸኛው የፌስቱላ ሆስፒታል የእርሳቸውን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።

የዶክተር ካትሪን ሃምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ሰኞ ይፈጸማል መባሉን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.