ሀገር አቀፍ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማጠቃለያ መርሐ-ግብር በአዳማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሀገር አቀፍ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማጠቃለያ እና የእውቅና መርሐ- ግብር በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ በሚል መሪ ቃል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር ባለፈው ሰኔ ወር ነበር የተጀመረው፡፡
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
በማህሌት ተ/ብርሃን