የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየመከረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በአርብቶ አደርና በከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ከሚገኙ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ምክክርና ዐውደ ጥናት እያካሔደ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ የምክክር ዐውደ ጥናቱን እያካሔደ የሚገኘው÷ ከጎንደር፣ ጋምቤላ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጂንካ፣ ሠመራ፣ ጅግጅጋና አሶሳ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ነው፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በመድኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደሩን የሕብረተሰብ ክፍል የተመለከተ ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰዋል፡፡
እነዚህ አካባቢዎች ዕምቅ የሆኑ ፀጋዎች ቢኖሯቸውም ፀጋዎቹ ተለይተው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ሚናቸው ዝቅተኛ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ይህንን ክፍተት ለመሙላትም ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር ምክክር ማድረግ አስፈልጓል ነው ያሉት፡፡
ሚኒስትሯ ዩኒቨርሲቲዎቹ በአርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶአደር አካባቢዎች የሚገኙ ፀጋዎችንና መልካም ዕድሎችን በተመለከተ ያካሄዷቸውን ምርምሮችና ወደ ተግባር የተቀየሩ ተግባራትን ገለጻ አድርገዋል፡፡
ሚኒስቴሩም እነዚህን መነሻዎች መሰረት በማድረግ የአካባቢዎቹን ማሕበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር ትስስር በመፍጠር በቅርበት እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!