Fana: At a Speed of Life!

በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መ/ቤትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነርና በአፍሪካ ሕብረት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ተወካይ ማረሰል ሲ. አክፖቮ እንዲሁም በተመድ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሰብዓዊ መብቶች ዋና አማካሪ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፔሪ ምቢቦንግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤትንና ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቸውም÷ የሰብዓዊ መብቶ ከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ  በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በዲጂታላይዜሽን የተከናወኑ የምርመራ ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት አራት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችን ገልጸውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ መምሪያው በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ያስመዘገባቸው ውጤቶችንም አብራርተውላቸዋል፡፡

ማረሰል ሲ. አክፖቮ ከተቋማዊ ለውጡ በፊት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ወቀሳዎች ይነሱበት እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ላይ ግን በምርመራ ሂደት የሚታየው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዓለም አቀፍ መስፈርትን የተከተለና ተጨባጭ ለውጦች መኖራቸውን አይተናል ብለዋል፡፡

የመጣው ለውጥ ሊደገፍና ሊበረታታ እንደሚገባው ጠቁመው÷ ለውጡን ለማስቀጠልም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.