Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያን የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትን የማሳደግ አዎንታዊ ሚና አለው – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት እና ህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያን የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ የኢንቨስትመንት አስፈጻሚ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በመድረኩ እንደተናገሩት የሰላም ስምምነቱ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የውጪ ባለሀብቶችን በብዛት ለመሳብ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥራል።

የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከምንም በላይ ሰላም የሚሻ ዘርፍ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ከሚሽነሩ፣ የውጪ ባለሀብቶች በአንድ ሀገር ኢንቨስት ለማድረግ የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ሰላም እና መረጋጋት መሆኑን ገልፀዋል።

የሰላም ስምምነቱ ተስፋ ሰጪ ከመሆኑም በላይ በኮቪድ እና በጦርነቱ የተቀዛቀዘውን የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት በቀጣይ ለማካካስ የሚያስችል አመቺ ዕድል እንደሚፈጥር መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.