ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን 811 ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት በጤና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን 811 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎች መካከል 351 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ 457ቱ ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሀሰን ዩሱፍ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተመራቂዎች በሰለጠኑበት ሙያ ህዝቡን በተነሳሽነትና በቅንነት እንዲያገለግሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡