የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ነቀምቴ ከተማን ጨምሮ ከምሥራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የጦር መኮንኖች፣ አባገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሸማግሌዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በክልሉ የሚታየው የጸጥታ ችግር ፣ መፈናቀልን፣ የንብረት ዘረፋን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች እንዳጋጠማቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
የመሰረተ ልማት ችግሮችን እና የሥራ አጥነትን ለመቅረፍ መንግሥት በትኩረት እንዲሠራም ነው ተሳታፊዎቹ የጠየቁት፡፡
በገላና ተስፋ