ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለሀገራችን እድገት ዋስትና ነው- የቡኖ በደሌ እና ጉጂ ዞኖች ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ እና ጉጂ ዞኖች የተለያዩ አካባቢዎች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
በሰልፉ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት ለሀገራችን እድገት ዋስትና ነው፣ መጋቢት 24 የመንግስትን ስርዓት በሴራና ሃይል የመቀየር አስተሳሰብን የዘጋ ታሪካዊ ቀን ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተደምጠዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው በዞኖቹ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!