ሀገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት ምስረታ መርሐ-ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት ምስረታ መርሐ-ግብር ተካሄደ፡፡
መርሐ-ግብሩ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ለወጣቶች ድምፅ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በምክር ቤት ምስረታው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ምክር ቤቱ ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን÷ በትናንትናው ዕለትም ምክር ቤቱን በቀጣዮቹ ጊዜያት የሚመሩ ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ አካላት ምርጫ አካሂዷል።
በዛሬው ዕለትም አባላቱን አቅርቦ በማፀደቅ ምክርቤቱ በይፋ ተቋቁሟል።
በትዝታ ደሳለኝና ማህሌት ተ/ብርሀን
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!