የዓለም ባንክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ከዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዲዮን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቸውም አቶ አሻድሊ በክልሉ ያለውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብት ሕዝቡን እንዲጠቅም በማድረግ ረገድ አበረታች ስራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡
የዓለም ባንክ በክልሉ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ሥራዎች ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
ኦስማኔ ዲዮን በበኩላቸው÷ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተመለከቷቸው የልማት ሥራዎች መደሰታቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ያለውን ሀብት በአግባቡ ማልማት ከተቻለ ለሀገር የሚጠቅም አቅም መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡
የዓለም ባንክ ለክልሉ ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!