Fana: At a Speed of Life!

  ቻይና ዜጎቿን ከሱዳን ልታስወጣ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ዜጎቿን ከሱዳን ልታስወጣ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እርምጃው በሱዳን የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የተወሰነ መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አመላክቷል።

ቻይና በካርቱም የሚገኙ ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ ማንኛውንም ጥረት እንደምታደርግም በቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ው ዢ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰሞኑ በአፍሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎችን እና ተቋማትን የደህንነት ሁኔታ ለማጠናከር የሚያስችል መመሪያ መስጠታቸው ይታወሳል።

በሱዳን ባለው ግጭት ሳቢያ የተለያዩ ሀገራት ዜጎቻቸውን እና ዲፐሎማቶቻቸውን እያስወጡ ሲሆን ቀደም ሲል አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ዜጎቿን በሰላም ማስወጣቷ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.