ከሠሃራ በታች ባሉ ሀገራት የጀርመን ጉዳይ አሥፈፃሚ በሱዳን ለተከሰተው ግጭት መፍትሄ ለመሻት ከኢጋድ ዋና ጸሐፊ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሠሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት እና በሳኅል ቀጠና የጀርመን የውጭ ጉዳይ አሥፈጻሚ ዳይሬክተር ክርስቶፍ ሬዝላፍ በሱዳን ለተከሰተው ግጭት መፍትሄ ለመሻት ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር) ጋር መክረዋል፡፡
ክርስቶፍ ሬዝላፍ ÷ በጉዳዩ ላይ ከኢጋድ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚመክሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
በሱዳን የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ መቆም እንዳለበትና ሁለቱን ወገኖች ለማስማማት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደሚያሻም አሳስበዋል፡፡