የጽንፈኝነትን ሰይጣናዊነት ያሳየ የግፍ ግድያ – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ጽንፈኝነት ብዙዎችን ሕዝብ ልጆች አሳጥቶናል። ጽንፈኞች ሰው ሆንን ይጠፋሉ።
ዛሬ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጸ/ቤት ኃላፊ እና ፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ግርማ የሺ ጥላ ባደገበት ቀየ በጽፈኞች በግፍ ተገድሏል። ይህም የጽንፈኛው ኃይል የመርዝ ፖለቲካ በቀየ የማይወሰን፣ ከጓዳ ጭምር ገብቶ ቤተሰብን የሚበትን ሆኑን አሳይቶናል።
ውዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ!
አጀንዳ አልባ የጥላቻ ፖለቲካ ዘርተው ጽንፈኝነት በማብቀል ልጆችህን በአደባባዩ የሚቀጥፉ የደም ነጋዴዎችን ማስቆም ካልቻልክ፣ የግፍ በትራቸውን የብዙኃኑን ቤት ማንኳኳቱ አይቀሬ ነው።
ዓላማቸው ማተራመስና ሀገራችንን ዕረፍት መንሣት የሆኑ አካላት አሉ። የእነዚህ አካላት አርአያዎቻቸው ዓለም አቀፍ አሸባሪዎች ናቸው። የእነርሱን ተግባር በኢትዮጵያ ለመድገምና ኢትዮጵያን ለማጥፋት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያልተፈጸሙ ዘግናኝ ተግባራትን ሁሉ ይፈጽማሉ።
ኢትዮጵያን ለማጽናትና ለማበልጸግ የጀመርነውን ትግል ጽንፈኞች አያስቆሙትም። ይሄንን ነውረኛ ዘግናኝ ተግባር የፈጸሙት የትም ቢገቡ ለሕግ ይቀርባሉ። ሌሎች በእነርሱ መንገድመ ጓዝ የጀመሩ በሕግ ማስከበር እዲቆሙ ይደረጋል።
ነብስህ በሰላም ትረፍ!
ሚያዝያ19 ቀን 2015 ዓ.ም