Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከተማ አቀፍ የመምህራን ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ “ትምህርት ቤት ለመማር፤ መምህራን ለማስተማር” በሚል መሪ ሐሳብ ከተማ አቀፍ የመምህራን የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ከ5 ሺህ በላይ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

የላቀ ውጤት እንዲመዘገብም በጋር መሥራት እንደሚገባ ጠቁመው÷ መደማመጥ ፣ መወያየትና ሁኔታዎችን ሰክኖ መመልከት ከመምህራን እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

በሀገር ግንባታ ውስጥ የመምህራን ሚና የጎላ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ አንስተዋል፡፡

መምህራን እያበረከቱት ላለው አስተዋጽዖም ምሥጋና ማቅረባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላት (ዶ/ር) ÷ መምህራን በሀገር ግንባታና ትውልድን በመቅረፅ ሂደት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.