Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻዎች ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆኑን የጀርመን ትራቭል አሶሴሽን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን ትራቭል አሶሴሽን የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻዎችና አማራጮች በጀርመን ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ÷ከጀርመን ትራቭል አሶሴሽን የፖሊሲና የውጪ ቱሪዝም ኃላፊ ቮልከር አዳምስ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ፍቃዱ የጀርመን ትራቭል አሶሴሽን የኢትዮጵያን ቱሪስት መዳረሻዎችን ለጀርመን የቱሪዝም ገበያ በሰፊው ለማስተዋወቅ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ በ10 ዓመት የመሪ ልማት እቅድ ከተቀመጡ አምስቱ የትኩረት መስኮች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው÷በሀገር ደረጃ ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ቮልከር አዳምስ በበኩላቸው ÷የኢትዮጵያን የቱሪዝም አማራጮች ለጀርመን ገበያ ለማስተዋወቅ 14 የጀርመን የጉዞ ወኪሎችና አስጎብኚ ድርጅቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ጠቁመዋል።

ልዑኩ የቱሪዝም ገበያ ጥናት ፎረም ኢትዮጵያ ላይ ለማካሄድ ማቀዱንም ነው ሃላፊው የተናገሩት።

የጀርመን ትራቭል አሶሴሽን አመራሮችን ያካተተ ልዑክም የቱሪዝም ጉብኝት በኢትዮጵያ በቅርቡ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

አሶሴሽኑ በጀርመን በሚገኙ 10 ሺህ የሚደርሱ የጉዞ ወኪሎች አማካኝነት የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻዎችና አማራጮች ለጀርመን ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆናቸውን ሃላፊው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.