የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን ሮም ከተማ በድንገት ሕይወቱ ያለፈው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቹ የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ።
በሀገር ፍቅር ቲዓትር ቤት የሙያ አጋሮቹ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ከተከናወነ በኋላ በመንበረ ፀባኦት ቅድስ ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ተፈፅሟል፡፡
በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አርቲስቶች፣ የአርቲስቱ ወዳጆች እና ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በምንተስኖት ሙሉጌታ