Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ በ“ላፕሴት” ፕሮጀክት ስብስባ ለመሳተፍ ጁባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ በ“ላፕሴት”ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ በደቡብ ሱዳን በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለመው ላፕሴት ፕሮጀክት አስመልክቶ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደሚሳተፍ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

የላፕሴት ፕሮጀክት በፈረንጆቹ 2012 በኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳን አገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ስራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.