Fana: At a Speed of Life!

የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሐካይንዴ ሒቺለማ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሐካይንዴ ሒቺለማ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንዲሁም የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.