ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ልትከፍት ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተለይም በንግድ፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በጸጥታ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸው ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ለመክፈት ስምምነት ላይ መደረሱን ምክትል ፕሬዚዳንቷ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡